إعدادات العرض
አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'
አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'
አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
ar bn bs en es fa id ru tl tr ur zh hi fr ug ku ha pt ml te sw my de ja ps vi as sq sv cs gu yo nl si ta prs bg ff hu kn ky lt or ro rw tg uz ak ne mos az wo om so uk km bm rn ka mk sr el mgالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ወንድሙ ላይ ያለውን ጥቂት መብቶች ገለፁ። ከነዚህ መብቶች መካከል የመጀመሪያው ሰላምታ ለሰጠህ ሰላምታን መመለስ ነው። ሁለተኛው መብት፡ ህመምተኛን መጠየቅና መዘየር ነው። ሶስተኛው መብት፡ ጀናዛን ከቤቱ ወደ ሚሰገድበት ከዚያም ወደ መቃብሩ ተወስዶ እስኪቀበር ድረስ መሸኘት ነው። አራተኛው መብት፡ ለሰርግም ይሁን ለሌላ ግብዣ ሲጠራ ጥሪውን አክብሮ ምላሽ መስጠት ነው። አምስተኛ መብት፡ ሲያስነጥስ "ተሽሚት" ሊያደርግ ሲሆን ይኸውም አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ትርጉሙም፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው) ካለ "የርሐሙከሏህ" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይዘንልህ) ይበለው፤ ከዚያም ያስነጠሰውም መልሶ "የህዲኩሙሏሁ ወዩስሊሕ ባለኩም" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይምራህ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) ይላል።فوائد الحديث
እስልምና በሙስሊሞች መካከል ያሉ መብቶችን በማበርታትና በመካከላቸው ያለን ወንድማማችነትና መዋደድን በማጠናከር በኩል ያለውን ልቅና ያስረዳናል።