'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'

'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'

ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ አንዳንድ ባሮቹን እንደሚወድ ገለፁ። ከነርሱም መካከል ፈሪሃ አላህ የሆነ አንዱ ነው። እርሱም:- የአላህን ትእዛዛት የሚተገብርና ክልከላዎቹን የሚርቅ ነው። ከሰዎች የተብቃቃንም ይወዳል። እርሱም:- በአላህ በመመካቱ የተነሳ ከሰዎች የተብቃቃና ከአላህ ውጪ ወደ ማንም የማይዞር ነው። ድብቅንም ይወዳል። እርሱም:- ለጌታው ባሪያና የሚተናነስ፣ በሚጠቅመው ነገር ላይ የሚጠመድ፣ ማንም እርሱን ማወቁም ይሁን ስለርሱ በሙገሳና ውዳሴ ማውራቱን ከቁብ የማይቆጥር ሰው ነው።

فوائد الحديث

አላህ ባሮቹን እንዲወድ የሚያስፈርዱ አንዳንድ ባህሪያቶች መገለፃቸውን እንረዳለን። እነርሱም:- አላህን መፍራት፣ መተናነስና አላህ የሰጠንን ወደን መቀበል ነው።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር