إعدادات العرض
አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በሱነኑል ኩብራ ፣ አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
ar bn bs en es fa fr id ru tl tr ur zh hi vi ku ha pt ml te sw my de ja ps as sq sv cs gu yo nl ug si ta prs ak az bg ff hu kn ky lt ne or ro rw tg uz mos wo om sr so bm uk rn km ka mk el mgالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምእመናን መካከል መስተጋብራቸውን ከሚያጠናክሩና በመካከላቸውም ውዴታን ከሚያሰፍኑ ሰበቦች መካከል አንዱን ጠቀሱ። ይኸውም አንድ ሰው ወንድሙን የሚወደው ከሆነ እንደሚወደው ይንገረው አሉ።فوائد الحديث
ለዓለማዊ ጥቅም ሳይሆን ጥርት ባለ መልኩ ለአላህ ብሎ መውደድ ያለውን ደረጃ እንረዳለን።
መዋደዱና መግባባቱ እንዲጨምር ለአላህ ብለው የሚወዱትን እንደሚወዱት መንገር እንደሚበረታታ እንረዳለን።
በምእመናን መካከል መዋደድ መስፋፋቱ ኢማናዊ የሆነውን ወንድማማችነት እንደሚያጠነክርና ማህበረሰቡንም ከመለያየትና ከመበታተን እንደሚታደግ እንረዳለን።