'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'

'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ 'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ ባሪያ ጌታውን በቸረውና ባጣቀመው ፀጋዎቹ ምክንያት ማመስገኑ የአላህ ውዴታን ከሚያገኝባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ስለሆነ ምግብ በልቶም "አልሐምዱሊላህ" ማለት ፤ የሚጠጣም ጠጥቶ "አልሐምዱሊላህ" ማለት እንደሚገባው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።

فوائد الحديث

አላህ ሲሳይን ችሮን በምስጋናችን በመደሰቱ የርሱን ችሮታ እንረዳለን።

የአላህ ውዴታ ከመብላትና መጠጣት በኋላ ማመስገንን በመሰለ ትንሽ ምክንያት እንኳ እንደሚገኝ እንረዳለን።

ከምግብና መጠጥ ስነስርአቶች መካከል ከበሉና ከጠጡ በኋላ አላህን ማመስገን አንዱ ነው።

التصنيفات

የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት, የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት