የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት)…

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት) ማለትን ያበዙ ነበር።

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት) ማለትን ያበዙ ነበር። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶና ይዘውት በመጡት ሃይማኖት አምነናል። በኛ ላይ የሚፈሩልን ጉዳይ አለ ማለት ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "አዎን ልቦች በአላህ ሁለት ጣቶች መካከል ናቸው። እንደፈለገው ይገለባብጣታል።" አሉኝ።»

[በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

አብዛኛው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓ በኢስላምና በአምልኮ ላይ መፅናትንና ከጥመት መራቅን አላህን የሚጠይቁበት ነበር። አነስ ቢን ማሊክም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህን ዱዓ በማብዛታቸው ተደነቀ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልቦች ከአላህ ጣቶች መካከል በሁለቱ ጣቶች መሀል እንደሆኑና እንደፈለገም እንደሚያገለባብጣቸው ነገሩት። ቀልብ የኢማንና ክህደት መኖሪያ ናት። ቀልብ ቀልብ ተብሎ የተሰየመው በብዛት ስለሚገለባበጥ ነው። ቀልብ ድስት በሚንተከተክ ጊዜ ከሚገለባበጠው በላይ ይገለባበጣል። አላህ ለሻለት ሰው ቀልቡን በቀናው መንገድ ላይና በኢስላም ላይ ያፀናለታል። አላህ ጥመት የሻለትን ሰው ደግሞ ቀልቡን ከቀናው መንገድ ወደ ጥመት ያዞርበታል።

فوائد الحديث

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጌታቸው ያላቸው መዋደቅና መተናነስን እንዲሁም ኡመታቸውም ይህንን ጥያቄ እንዲጠይቁ መጠቆማቸውን እንረዳለን።

በኢስላም ላይ የመፅናትና ቀጥ የማለት አንገብጋቢነቱን እንረዳለን። ዋናው ቦታ የሚሰጠውም ፍፃሜያችን ነው።

አንድ ባሪያ በኢስላም ላይ መፅናትን ከአላህ ከመፈለግ ለአይን ጨረፍታ ያህል እንኳ አይብቃቃም።

ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተከትለን ይህንን ዱዓ በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

በእስልምና ላይ መፅናት አንድ ባሪያ ሊለፋለት የሚገባና በርሱም ጌታውን ሊያመሰግንበት የሚገባ ትልቁ ፀጋ ነው።

التصنيفات

በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች, የቀልብ ተግባራት