በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች

በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች

4- ረቢግፊርሊ ኸጢአቲ፣ ወጀህሊ፣ ወኢስራፊ ፊ አምሪ ኩሊህ፣ ወማ አንተ አዕለሙ ቢሂ ሚኒ፣ አላሁምመግፊርሊ ኸጧያየ፣ ወዓምዲ፣ ወጀህሊ፣ ወሀዝሊ ወኩሉ ዛሊከ ዒንዲ፤ አላሁመግፊርሊ ማ ቀደምቱ፣ ወማ አኸርቱ፣ ወማ አስረርቱ፣ ወማ አዕለንቱ፤ አንተል ሙቀዲሙ፣ ወአንተል ሙአኺሩ፣ ወአንተ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙም "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን፣ አለማወቄን፣ በሁሉም ነገር ወሰን ማለፌን፣ አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ። አላህ ሆይ! ወንጀሌን፣ ሆን ብዬ የሰራሁትን፣ አለማወቄን፣ ቀልዴን ማረኝ፤ ይህ ሁሉም ከኔው ነው። አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን፣ ያዘገየሁትን፣ የመሰጠርኩትን፣ ግልፅ ያወጣሁትን ወንጀል ማረኝ፤ አንተ አስቀዳሚ ነህ፣ አንተም የሚያዘገይ ነህ፣ አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።" ማለት ነው።