إعدادات العرض
አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።
አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።
ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች አሉ። በየሁሉም ደረጃዎች መካከል በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ርቀት ያህል አለ። ፊርደውስ የላይኛው ደረጃ ነው። የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ ነው። ከላዩዋ ያለውም (ጣሪያዋ) ዐርሽ ነው። አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።"
الشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመጪው አለም ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች እንዳሉ፤ በየሁሉም ደረጃዎች መካከል የሚገኘው ርቀት በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ያህል ርቀት እንደሆነ፤ ከነዚህ ጀነቶች መካከል ከፍተኛዋ ጀነት ፊርደውስ እንደሆነች፤ አራቱ የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ መሆኑን፤ ከፊርደውስ በላይም ዐርሽ መሆኑንና ፊርደውስም ከሁሉም ጀነቶች በላይ ስለሆነች አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት ብለው ተናገሩ።فوائد الحديث
የጀነት ነዋሪዎች በደረጃ እንደሚበላለጡና ይህም በኢማንና በመልካም ስራዎቻቸው ልክ እንደሆነ እንረዳለን።
አላህን ከጀነት ሁሉ ላእላይ የሆነችውን ፊርደውስ እንድንጠይቀው መነሳሳቱን እንረዳለን።
ፊርደውስ የጀነት ላይኛዋና በላጯ እንደሆነች እንረዳለን።
ሙስሊም የሆነ ሰው ከፍ ያለ አላማ ሊኖረው እንደሚገባና አላህ ዘንድ የላቀ የሆነንና በላጭ የሆነን ደረጃ ለማግኘት መልፋትና መጣር እንደሚገባው እንረዳለን።
ጀነት አራት ወንዞች አሏት: እነርሱም: የውሃ፣ የወተት፣ ወይን ጠጅና የማር ናቸው። እነዚህም በዚህ የአላህ ንግግር ውስጥ በቁርአን ተጠቅሰዋል። {የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ጀነት ምሳሌ በውስጧ ሽታውን ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከሆነች የወይን ጠጅም ወንዞች፣ ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት።} [ሙሐመድ: 15]