إعدادات العرض
በመጨረሻው ቀን ማመን
በመጨረሻው ቀን ማመን
1- ‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›
2- በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።
3- ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።
4- ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም።
5- አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ ወደ አንዱ በአልጋው ላይ እንደተደገፈ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው
6- የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
7- አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም
8- የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።
11- አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል።
12- ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።
14- ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።
21- አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል
23- አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
24- አይሁዶችን ሳትዋጉና ከኋላው አንድ አይሁድ የተደበቀበት ድንጋይ ሙስሊሙ ሆይ! ይህ አይሁድ ከኋላዬ አለ ግደለው ሳይል ሰዓቲቱ አትቆምም።
26- ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ
27- ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
28- 'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'
29- የሐውዴ ( ኩሬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ
31- የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው።
32- ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል
33- የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።
35- ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
36- ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?
37- {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።}
38- በመጨረሻዎቹ ሕዝቦቼ (ኡመቴ) ውስጥ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ያልሰማችሁትን የሚነግሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ። አደራችሁን አደራችሁን ተጠንቀቋቸው።
39- ሙአዚኑን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።