إعدادات العرض
ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ…
ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው። አይሸኑም፤ ሰገራም አይወጣቸውም፤ አይተፉም፤ አይናፈጡም። ማበጠሪያቸው ወርቅ ነው፤ ላባቸው ሚስክ ነው፤ እጣን ማጤሻቸው ምርጥ መአዛ ያለው እንጨት የ 'ኡሉወቱል አንጁጅ' ነው፤ ሚስቶቻቸው ሑሩል ዒን ናቸው። ጀነት ሲገቡ ልክ እንደ አንድ ሰው አፈጣጠር በአባታቸው አደም ቅርፅ ላይ ሆነው ነው የሚገቡት። ቁመታቸው ስልሳ ክንድ ሆነው ነው የሚገቡት።"»
الشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው የአማኞች ህብረት ጨረቃ ሙሉ እንደምትሆንበት ምሽት ፊቶቻቸው እያበራ እንደሆነ፤ ከነርሱ ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ ውበታቸው ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ እንደሆነ፤ እንዲሁም የጀነት ሰዎች የተሟላ ባህሪያት እንዳላቸው ይህም የማይሸኑ፤ ሰገራ የማይወጣቸው፤ የማይተፉና የማይናፈጡ መሆናቸውን፤ ማበጠሪያቸውም ወርቅ፤ ላባቸው ሚስክ፤ ከእጣን ማጨሻቸው የሚወጣው መአዛ ምርጥ መአዛ ያለው እጣን እንደሆነ፤ ሚስቶቻቸው ሑሩል ዒን ናቸው። በአፈጣጠርና ቁመትም ልክ እንደ አንደሰው የአባታቸውን አደም ቅርፅ ይዘው እንዳላቸውና የአደም ሰውነት ርዝማኔም ስልሳ ክንድ እንደሆነ ተናገሩ።فوائد الحديث
የጀነት ሰዎች ባህሪ መገለፁንና እነርሱም እንደየደረጃቸውና ስራዎቻቸው እንደሚበላለጡ ተረድተናል።
ሀሳቦችን ለማስረዳትና ለማብራራት ምሳሌዎችን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: "የጀነት ሰዎች ፂም የሌላቸውና ፀጉራቸውም የማይቆሽሽ ከመሆኑ ጋር ማበጠሪያ ለምን ያስፈልጋቸዋል? መአዛቸው ከሚስክ የበለጠ ምርጥ ሆኖ ሳለ እጣንስ ለምን ያስፈልጋቸዋል? የሚል ጥያቄ ከተነሳ: የጀነት ሰዎች ፀጋ መብላቱም፣ መጠጣቱም፣ መልበሱም፣ ሽቶውም በረሃብ ወይም በጥም ወይም በመራቆት ወይም በመቆሸሽ ህመም ምክንያት የሚጠቀሙት አይደለም። የጀነት ፀጋ የተከታተለ እርካታና የተነባበረ ፀጋ ስለሆነ ነው። የዚህም ጥበብ ዱንያ ላይ ይጣቀሙበት በነበረው አይነት እንዲጣቀሙ ነው። ተብሎ ይመለሳል።"