የሐውዴ (የምንጬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ

የሐውዴ (የምንጬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ

ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "የሐውዴ (የምንጬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ፣ የብርጭቆዎቹ ብዛት የሰማያት ኮኮቦች ያህል ናቸው። ከሷ አንዴ የጠጣ ከቶም መቼም አይጠማም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የውመል ቂያማ የሚሰጣቸው ምንጭ እንዳለ እንዲሁም እርዝማኔውና ጎኑ አንድ ወር እንደሚያስኬድ ተናገሩ። ውኃው ከወተት እጅግ የበለጠ ንጣት እንዳለው፤ ሽታው ከሚስክ መአዛ የበለጠ ምርጥና ማራኪ መአዛ እንዳለው፤ የብርጭቆዎቹ ብዛት አምሳያ የሰማይ ኮኮቦች ያህል እንደሆነ፤ በዚህ ብርጭቆ ከምንጩ የጠጣ ሰው መቼም እንደማይጠማ ተናገሩ።

فوائد الحديث

የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምንጭ የውመል ቂያማ ከሳቸው ኡመት የሆኑ አማኞች ለመጠጣት የሚወርዱበት የግዙፍ ውኃ ጥርቅም ነው።

ከምንጩ የሚጠጣ ሰው መቼም ያለመጠማት ፀጋን እንደሚያገኝ እንረዳለን።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን