ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?

ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?

ቀታዳህ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደነገሩን አንድ ሰው "የአላህ ነቢይ ሆይ! ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀሳሉ?" አላቸው። እርሳቸውም " ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" አሉት። ቀታዳህ እንዲህ አሉ፦ "በጌታዬ ልቅና ይሁንብኝ እንዴታ!"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀላሉ?" ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው አላህ የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" በማለት መለሱ። አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።

فوائد الحديث

የትንሳኤ ቀን የከሀዲያን ውርደት፤ ከሀዲ በፊቱ እየተሳበ ነው የሚሄደው።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን, አላህን በጌትነቱ መነጠል, አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል