አዛን አድራጊዎች የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች ናቸው።

አዛን አድራጊዎች የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች ናቸው።

ከሙዓዊያህ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አዛን አድራጊዎች የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለሶላት የሚጣሩ አዛን አድራጊዎች ስራቸው የላቀ፣ መልካማቸው የበዛና ምንዳቸው የገዘፈ በመሆኑ የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች እንደሚሆኑ ተናገሩ።

فوائد الحديث

የአዛን ትሩፋቶችና አዛን በማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

የአዛን ባዮች ልቅናና የትንሳኤ ቀን ደረጃቸው ከፍ ያለ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።

التصنيفات

የመጨረሻው ህይወት, አዛንና ኢቃማህ