إعدادات العرض
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
ዚያድ ቢን ለቢድ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።
[በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Kurdî Wolof Soomaali Français Oromoo Azərbaycan Tagalog Українська mr தமிழ் bm Deutsch ქართული Português Македонски Magyar Lingala Русский 中文الشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በባልደረቦቻቸው መሀል ተቀምጠው ሳለ እንዲህ አሉ፦ "ይህ ወቅት እውቀት ከሰዎች የሚነጠቅና የሚነሳበት ወቅት ነው።" ይህኔ ዚያድ ቢን ለቢድ አልአንሷሪይ በመደነቅ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጠየቁ። እንዲህም አሉ፦ "ቁርኣንን ቀርተነዋል፣ በቃላችን ሸምድደነዋል በአላህ እምላለሁ! እንቀራዋለን፣ ሴቶቻችንንም ልጆቻችንንም፣ የልጅ ልጆቻችንንም እያስቀራነው እንዴት ዕውቀት ይነሳል ከኛ እንዴት ይጠፋል?!" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመደነቅ እንዲህ አሉ: "ዚያድ ሆይ! እናትህ ትጣህና ከመዲና ነዋሪዎች ውስጥ ከሚገኙ ዐሊሞች እቆጥርህ ነበርኩ።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሱ ዕውቀት የሚጠፋው ቁርኣን በመጥፋቱ እንዳልሆነ ነገር ግን ዕውቀት የሚጠፋው በዕውቀት መሥራት ሲጠፋ እንደሆነ አብራሩለት። ተውራትና ኢንጂል አይሁዶችና ክርስቲያኖች ዘንድ አለ። ከዚህም ጋር ምንም አልጠቀማቸውምም የታለመለትንም ግብ አላሳኩም። የታለመለት ዓላማ ባወቁት መሥራት ነበርና።فوائد الحديث
ቁርኣንና መጽሐፎች በሰዎች እጅ መኖራቸው ብቻ ካልተሰራባቸው በስተቀር ምንም አይፈይዱም።
የዕውቀት መጥፋት በተለያየ መልኩ ይከሰታል። ከነሱም ውስጥ: - የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሞት፣ የዑለሞች ሞት፣ በዕውቀት መስራት መተው ይጠቀሳሉ።
ከሰዓቲቱ ምልክቶች ውስጥ የዕውቀት መጥፋትና በሱ አለመስራት ይጠቀሳል።
በዕውቀት መሥራት ላይ መነሳሳቱ እሱ ነውና ዋናው የተፈለገው።