إعدادات العرض
አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە සිංහල हिन्दी Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Türkçe Tiếng Việt नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Bosanski Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Kurdî Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Mooreالشرح
ሰውዬው በቀብር በኩል እያለፈ ሞቶ በተቀበረው ፋንታ ሞቶ በነበር እስኪመኝ ድረስ ሰአቲቱ እንደማትቆም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። የዚህ ምክንያትም ጥመትና የጥመት ባለቤቶች በመብዛታቸው፣ ፈተና፣ ወንጀልና ውግዝ ተግባራት ይፋ በመሆናቸው ሳቢያ ኢማኑ እንዳይጠፋ በነፍሱ ላይ በመፍራቱ ነው።فوائد الحديث
በመጨረሻው ዘመን ወንጀሎችና ፈተናዎች ይፋ እንደሚሆኑ መጠቆሙን እንረዳለን።
ጥንቃቄ በማድረግ፣ በኢማንና በመልካም ስራ ለሞት መዘጋጀት እና ከፈተናና መከራ ስፍራዎች መራቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።