ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው…

ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው እስከማይቀበለው ድረስም ገንዘብ (ሀብት) ይበዛ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው እስከማይቀበለው ድረስም ገንዘብ (ሀብት) ይበዛ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመርየም ልጅ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል በነቢያችን ድንጋጌ በፍትህ ሊፈርዱ መውረጃ ጊዜያቸው ቅርብ እንደሆነ ምለው ተናገሩ። በሚመጡ ወቅትም ክርስቲያኖች የሚያልቁትን መስቀል ይሰባብራሉ፤ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አሳማዎችንም ይገድላሉ፤ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግብርንም ያስቀራሉ፤ ሰዎች ባጠቃላይ ወደ ኢስላም እንዲገቡም ይታገላሉ፤ ገንዘብ (ሀብት) ይትረፈረፋል አንዱ ከሌላው አይቀበለውም። ይህም ገንዘብ ከመብዛቱ፣ ሁሉም እያንዳንዱ እርሱ ዘንድ ባለው ገንዘብ የተብቃቃ ከመሆኑ፣ በረካ ሰፍኖ መልካምነትም ከመከታተሉ አኳያ ነው።

فوائد الحديث

ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመጨረሻ ዘመን እንደሚወርዱ መረጋገጡንና የርሳቸው መምጣት የትንሳኤ ቀን ምልክት መሆኑን እንረዳለን።

የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድንጋጌ የሚሽር ሌላ ድንጋጌ እንደሌለ እንረዳለን።

በመጨረሻ ዘመን ሰዎች ከገንዘብ ቸልተኛ ከመሆናቸውም ጋር የገንዘብ በረከት ግን እንደሚሰፍን እንረዳለን።

በመጨረሻ ዘመን ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢስላም ሃይማኖት ስለሚፈርዱ ኢስላም ዘውታሪ ሃይማኖት መሆኑ መበሰሩን እንረዳለን።

التصنيفات

ቀዳሚ መልክተኞችና ነቢያቶች የአላህ ሰላም ይስፈንባቸው።, ነቢያችን ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና, የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት, የኢስላም ሃይማኖት በጥቅሉ