አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።

አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት አዛን የሚያደርግን ሰው የሰማ ከ"ሐይየዐለተይን" ውጪ ከኋላው አስከትሎ (ሙአዚኑ) የሚለውን አምሳያ እንዲል ጠቆሙ። ከ"ሐይየዐለተይን" በኋላ ግን "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" ይላል። አዛኑ ከተጠናቀቀ በኋላም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላትን ያወርዳል። እነሆ በርሳቸው ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶላት ያወርድበታልና። አላህ በባሪያው ላይ ሶላት አወረደ ማለት መላኢኮች ዘንድ ባሪያውን ማወደሱ ነው። ቀጥለውም አላህ ወሲላን ለሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲሰጣቸው እንድንጠይቅ አዘዙ። እርሷም በጀነት ውስጥ የምትገኝ ከፍተኛዋ ደረጃ ናት። ይህቺ ስፍራም ከሁሉም የአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ ለማንም አትሰጥም አትበጅምም (አትገባም)። ያ ባሪያ እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ የተናገሩት ለመተናነስ ብለው ነው እንጂ ይህቺ ከፍተኛ ደረጃ ለአንድ ባሪያ እንጂ ለማንም የማትሆን ከሆነች ያ አንድ ባሪያ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንጂ ማንም አይሆንም። እሳቸው ከፍጡራን ሁሉ በላጩ ፍጡር ናቸውና። ቀጥለው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን ከአሏህ የለመነ ሰው የርሳቸውን ምልጃ እንደሚያገኝ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።

فوائد الحديث

የሙአዚንን ጥሪ በመመለስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ለሙአዚን ከመለስን በኋላ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላት የማውረድን ትሩፋት እንረዳለን።

ሶላት ካወረድንባቸው በኋላ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

የወሲላ ምንነትና ጉዳዩዋ ከፍ ያለ መሆኑ መገለፁ። ለአንድ ባሪያ እንጂ አትበጅምና (አትገባም)።

በዚህች ከፍተኛ ደረጃ በመነጠላቸው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ደረጃ መገለፁ።

ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአሏህ ወሲላን የጠየቀላቸው ሰው የርሳቸው ምልጃ ትፀድቅለታለች።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ደረጃ የርሳቸው ከመሆኗም ጋር ኡመታቸው ዱዓ እንዲያደርጉላቸው መፈለጋቸው ትህትናቸውን ይገልፃል።

መልካም ስራ በአስር መባዛቱ የአላህ ትሩፋትና እዝነት ስፋቱን ያስረዳናል።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን, የዚክር ትሩፋቶች, አዛንና ኢቃማህ