إعدادات العرض
በመጨረሻዎቹ ሕዝቦቼ (ኡመቴ) ውስጥ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ያልሰማችሁትን የሚነግሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ። አደራችሁን አደራችሁን ተጠንቀቋቸው።
በመጨረሻዎቹ ሕዝቦቼ (ኡመቴ) ውስጥ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ያልሰማችሁትን የሚነግሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ። አደራችሁን አደራችሁን ተጠንቀቋቸው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "በመጨረሻዎቹ ሕዝቦቼ (ኡመቴ) ውስጥ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ያልሰማችሁትን የሚነግሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ። አደራችሁን አደራችሁን ተጠንቀቋቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Shqip Soomaali Српски Українська Wolof Tagalog Moore Malagasy தமிழ்الشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመጨረሻዎቹ ኡመታቸው ውስጥ ውሸትን የሚቀጥፉ ሰዎች ብቅ እንደሚሉ ተናገሩ። ከነርሱ በፊት አንድም ሰው ያልተናገረውን ይናገራሉ፤ የተዋሹና የተቀጠፉ ሐዲሦችን ይናገራሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነርሱ እንድንርቅና እንዳንቀማመጣቸው፣ ከርሱ መራቅ እስኪያቅተን ድረስ ይህ የተቀጠፈ (የተፈበረከ) ሐዲሥ ነፍስ ውስጥ ተፅዕኖ እንዳያሳድርብንም ሐዲሣቸውን አለመስማትን አዘዙን።فوائد الحديث
እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከነቢይነት ምልክቶች አንዱ ምልክት አለ። ይኸውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ውስጥ ለወደፊት የሚከሰትን ተናገሩ እንዳሉትም መከሰቱ ነው።
በአላህ መልዕክተኛ ላይ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲሁም በኢስላም ላይ የሚዋሽን ሰው መራቅና ውሸታቸውን አለመስማት እንደሚገባ እንረዳለን።
ቅቡልነቱንና ትክክለኛነቱን እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ እንጂ ሐዲሦችን ከመቀበልም ከማሰራጨትም መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።