እኔ ሐውድ (ኩሬ) ላይ ሁኜ ከናንተ መካከል ወደ እኔ የሚመጣን እመለከታለሁ። በአቅራቢያዬ ያሉ ሰዎች (እንዳይጠጡ) ይያዛሉ። እኔም "ጌታዬ ከኔ ከኡመቴ ናቸው’እኮ

እኔ ሐውድ (ኩሬ) ላይ ሁኜ ከናንተ መካከል ወደ እኔ የሚመጣን እመለከታለሁ። በአቅራቢያዬ ያሉ ሰዎች (እንዳይጠጡ) ይያዛሉ። እኔም "ጌታዬ ከኔ ከኡመቴ ናቸው’እኮ

አስማእ ቢንት አቢበክር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "እኔ ሐውድ (ኩሬ) ላይ ሁኜ ከናንተ መካከል ወደ እኔ የሚመጣን እመለከታለሁ። በአቅራቢያዬ ያሉ ሰዎች (እንዳይጠጡ) ይያዛሉ። እኔም "ጌታዬ ከኔ ከኡመቴ ናቸው’እኮ" እላለሁ። ለኔም፦ "ከአንተ ህልፈት በኋላ የሠሩትን ታውቃለህን? በአላህ እምላለሁ (ከእምነታቸው) ወደ ኋላ ከማፈግፈግ አልተወገዱም።" እባላለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን ከኡመታቸው መካከል ወደ ኩሬያቸው የሚመጣን ሰው ለመመልከት ከኩሬያቸው ላይ እንደሚሆኑ ገለፁ። ከሳቸው አቅራቢያም ሰዎች እንዳይጠጡ ይያዛል። እርሳቸውም፦ "ጌታዬ ሆይ እነሱ ከኔ ኡመት እኮ ናቸው" ይላሉ። ለርሳቸውም፦ "አንተን ከተለያዩ በኋላ የሰሩትን ታውቃለህን? በአላህ እምላለሁ ወደኋላቸው ከመመለስና ከእምነታቸው ከማፈንገጥ አልተወገዱም። ከአንተም አይደሉም ከኡመትህም አይደሉም።" ተብሎ ይመለስላቸዋል።

فوائد الحديث

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለኡመታቸው ያላቸው እዝነትና ስለ ተከታዮቻቸው ያላቸው ጉጉት፤

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የነበሩበትን መንገድ መቃረን አደገኝነት፤

የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሱና አጥብቆ በመያዝ ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን, የመጨረሻው ህይወት, የኢማን ቅርንጫፍ