'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'

'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን አላህ ምድርን እንደሚጨብጥና እንደሚሰበስባት፤ ሰማይንም ከፊሉን ከከፊሉ በላይ አድርጎ በቀኝ እጁ እንደሚጠቀልልና ገፍፎ እንደሚያጠፋቸው ከዚያም "እኔ ነኝ ንጉስ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!" እንደሚል ተናገሩ።

فوائد الحديث

የአላህ ንግስና ዘውታሪ፤ የሌላው ንግስና ግን ጠፊ መሆኑን ማስታወስ እንደሚገባ እንረዳለን።

የአላህን ግርማዊነት፣ የችሎታውና ስልጣኑ ልቅና እንዲሁም የንግስናውን ምሉዕነት እንረዳለን።

التصنيفات

በአላህ ማመን, በመጨረሻው ቀን ማመን, አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል