በአላህ ማመን

በአላህ ማመን

9- አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም አልፎ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎች ይጽፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።