إعدادات العرض
ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም
ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም
ከዓዲይ ቢን ሓቲም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም ወደ ቀኝ ይመለከታል። ያሳለፈውን እንጂ ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራም ይመለከታል ካሳለፈው በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ይመለከታል በፊትለፊቱ ከእሳት ውጭ ሌላ ምንም አይመለከትም። በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን እሳትን ተጠንቀቁ።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog Tiếng Việt Kurdî Português සිංහල Русский অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી Nederlands پښتو Hausa नेपाली ไทย മലയാളം Кыргызча Română Svenska Malagasy Shqip Српски తెలుగు ქართული Moore Magyar Македонскиالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም አማኝ የትንሳኤ ቀን ብቻውን አላህ ፊት እንደሚቆምና አላህም ማንም በመካከላቸው ንግግሩን የሚተረጉም አስተርጓሚ ሳይኖር እንደሚያናግረው ተናገሩ። ከፊት ለፊቱ ካለችው እሳት ለመዳን የሚሄድበት መንገድ ያገኝ እንደሁ በሚል በድንጋጤ ብዛት ወደ ግራና ቀኝ አቅጣጫ እንደሚመለከትም ተናገሩ። ወደ ቀኝ አቅጣጫ ሲመለከትም ካሳለፈው መልካም ስራ በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራ አቅጣጫ ሲመለከትም ካሳለፈው መጥፎ ስራ በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ሲመለከትም ከእሳት በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። በሲራጥ ላይ ማለፍ የግዱ ስለሆነበት እሳትን ወደ ጎን አድርጎ መተውም አልተቻለውም። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተምር ክፋይን የምታህል ትንሽ ነገር እንኳ በመመፅወት በናንተና በእሳት መካከል የሚከልል የመልካም ስራና የምፅዋት ጋሻ አዘጋጁ አሉ።فوائد الحديث
ብታንስ እንኳ ምፅዋት በመስጠት ላይ፣ ምስጉን ባህሪያትን በመላበስ ላይ፣ ንግግርን አለስልሶ በመኗኗር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
የፍርዱ ቀን አላህ ወደ ባሮቹ በመካከላቸው ግርዶሽ፣ አማካኝና አስተርጓሚ ሳይኖር የሚቀርብ መሆኑን እንረዳለን። ስለዚህም የትኛውም አማኝ የጌታውን ትእዛዝ ከመቃረን መጠንቀቅ ይገባዋል።
አንድ ሰው የሚመፀውተው ነገር ትንሽ እንኳ ብትሆን ከእሳት መጠበቂያው ልትሆን ስለምትችል ሊያሳንሳት እንደማይገባው እንረዳለን።