አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።

አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ወደ ሰዎች ቅርፅና ሰውነት ያምራል ወይስ አስቀያሚ? ትልቅ ወይስ ትንሽ? ጤነኛ ወይስ በሽተኛ? በማለት እንደማይመለከት ገለፁ። ወደ ገንዘቦቻቸውም ብዙ ወይስ ትንሽ? በማለት አይመለከትም። አላህ ባሮቹን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ባላቸው መበላለጥ ተንተርሶ አይቀጣቸውምም አይተሳሰባቸውምም። ነገር ግን በቀልቦቻቸው ውስጥ ወዳለው ፍራቻ፣ የእምነት እርግጠኝነት፣ እውነተኝነት፣ ኢኽላስ (ፍፁማዊነት) ወይም የይዩልኝ ፣ የይስሙልኝ አስተሳሰብ ነው የሚመለከተው። ወደ ስራዎቻቸው ከመስተካከሏና ከመበላሸቷ አንፃር ይመለከትና በዛም መሰረት ይመነዳል።

فوائد الحديث

ቀልብን ከሁሉም ውግዝ ባህሪያት ማስተካከልና ማፅዳት ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለብን፤

ቀልብ የሚስተካከለው በኢኽላስ ሲሆን ስራ የሚስተካከለው ደግሞ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመከተል ነው። አላህ ዘንድ ትኩረት የሚቸራቸውና ግምት ውስጥ የሚገቡት እነዚህ ሁለቱ ናቸው።

የሰው ልጅ በገንዘቡም፣ በውበቱም፣ በሰውነቱም ሆነ በዚህች ዓለማዊ መገለጫዎች በአንዳችም ነገር መሸወድ እንደሌለበት ፤

ውስጣዊ ማንነትን ሳያስተካክሉ ውጫዊ የሆኑ መገለጫዎችን ከመደገፍ መጠንቀቅ እንዳለብን ተረድተናል።

التصنيفات

አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል, የቀልብ ተግባራት