'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'

'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'

ከጧሪቅ ቢን አሽየም አልአሽጀዒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: 'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

በምላሱ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ያለና የመሰከረ ሰው ፤ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደና ከኢስላም ውጪ ካሉ ሁሉ እምነቶች የጠራ ሰው በሙስሊሞች ላይ ገንዘቡና ደሙ እርም ይሆናል። እኛ ውጫዊ ከሆኑ ስራዎቹ በስተቀር መፈላፈል አይፈቀድልንም። በኢስላማዊ ህግጋት ይህንን የሚያስገድድ አስገዳጅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ገንዘቡም እንደማይነጠቅ ደሙም እንደማይፈስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። የትንሳኤ ቀን ሂሳቡን በበላይነት የሚመራው አሏህ ነው። እውነቱን ከሆነ ይመነዳዋል። ሙናፊቅ ከሆነ ደግሞ ይቀጣዋል።

فوائد الحديث

"ላኢላሃ ኢለሏህ" ብሎ መናገርና ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ሁሉ መካድ ወደ ኢስላም ለመግባት መስፈርት ነው።

የ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ትርጉም በጣኦታት፣ በመቃብሮችና በሌሎችም ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ሁሉ መካድና በአምልኮ እሱን ብቻ መነጠል ነው።

ተውሒድን የተገበረና በውጫዊ ማንነቱ የአላህ ድንጋጌዎች ላይ የፀና ይህን የሚፃረር ነገር ከሱ ይፋ እስካልሆነ ድረስ እርሱን ከመተናኮል መቆጠብ ግዴታ ነው።

የሙስሊም ገንዘብ፣ ደሙና ክብሩ የተከበረ ስለሆነ በሸሪዓዊ ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር እነዚህን መዳፈር እንደማይፈቀድ እንረዳለን።

በዱንያ ውስጥ ፍርድ የሚሰጠው በውጫዊ ማንነት ሲሆን በአኺራ ደግሞ ኒያዎችና አላማዎች ላይ በመንተራስ ነው።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል