إعدادات العرض
ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'
ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'
ከአቡ ዋቂድ አል-ለይሢይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፉት: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን የወጡ ጊዜ 'ዛቱ አንዋጥ' በምትባል የአጋርያን ዛፍ በኩል አለፉ። በርሷ ላይ (በረከትን በመፈለግ) መሳሪያዎቻቸውን ያንጠለጥሉባት ነበር። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለነርሱ ‹ዛቱ አንዋጥ› እንዳላቸው ለኛም (የምናንጠለጥልበት) ‹ዛቱ አንዋጥ› አድርግልን።' አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ 'ለአላህ ጥራት ተገባው! ይህ (የተናገራቹት) የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} [አል አዕራፍ: 138] ብለው እንደተናገሩት ነው። ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย മലയാളം Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolofالشرح
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን ወጡ። ሑነይን: በጧኢፍና መካ መካከል የሚገኝ ሸለቆ ነው። ከርሳቸውም ጋር የሚጓዙ በቅርብ ወደ ኢስላም የገቡ የተወሰኑ ሶሐቦች ነበሩ። "ዛቱ አንዋጥ" ማለትም የመንጠልጠያ ባለቤት በምትባል ዛፍ በኩል አለፉ። ዛፊቱ አጋርያን ያልቋትና መሳሪያዎቻቸውንና ሌሎች ነገሮችንም በረከትን በመፈለግ የሚያንጠለጥሉባት ዛፍ ነበረች። ከመልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነርሱ በረከትን ለመፈለግ መሳሪያዎቻቸውን የሚያንጠለጥሉበት የርሷ አምሳያ ዛፍ እንዲያደርጉላቸው ፈለጉ። ይህም የሚፈቀድ ነገር ስለመሰላቸው ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ንግግራቸው እያወገዙ አላህን በማላቅ ተስቢሕ አደረጉ። ይህ ንግግር የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} በማለት ለሙሳ የተናገሩትን ንግግር እንደሚመስልም ተናገሩ። የሙሳ ህዝቦች ጣኦት የሚያመልክን በተመለከቱ ጊዜ አጋርያን ጣኦት እንዳላቸው ለነርሱም ጣኦት እንዲኖራቸው ፈለጉ። ይህ ግን የነርሱን መንገድ መከተል ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ህዝብ የየሁዶችንና የክርስቲያኖችን መንገድ እንደሚከተልና የነርሱን ድርጊት እንደሚፈፅም በማስጠንቀቅ መልኩ ተናገሩ።فوائد الحديث
የሰው ልጅ አንዳንዴ አንዳች ነገር ከአሏህ የሚያርቀው ሆኖ ሳለ ወደ አላህ የሚያቃርበው እንደሆነ አድርጎ ሊያስበው ይችላል።
አንድ ሙስሊም በሃይማኖት በኩል ሊባል የማይገባን ነገር የሰማ ጊዜና የተደነቀ ጊዜ ተስቢሕና ተክቢር ማድረግ ይገባዋል።
ከሺርክ መካከል በዛፍ፣ በድንጋይና በሌሎች ነገሮች በረከት መፈለግ አንዱ ነው። በረከት የምንፈለገው ከአላህ ብቻ ነው።
የጣኦት አምልኮ መንስኤው ጣኦትን ማላቅ፣ እርሱ ዘንድ አዘውትሮ መቀመጥና በርሱ በረከትን መፈለግ ነው።
ወደ ሺርክ የሚያዳርሱ መንገዶችንና በሮችን መዝጋት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በቁርአንና ሐዲሥ ውስጥ አይሁድና ክርስትያኖችን በማውገዝ የመጡ ጥቅሶች ለኛ ማስጠንቀቂያ ናቸው።
የኛ እምነት አካል መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃ እስካልመጣ ድረስ ከድንቁርና ዘመን ሰዎች፣ ከየሁዶችና ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።
التصنيفات
አላህን በተመላኪነቱ መነጠል