إعدادات العرض
በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'
በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'
ከአቡ በሺር አል አንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: እርሱ በአንድ ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ነበርና እንዲህ አለ: "ሰዎች በማደሪያቸው ባሉበት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን የሚያውጅ) አንድ መልክተኛ ላኩ ' በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە සිංහල دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Wolof Soomaali Moore Українська Български Azərbaycan ქართული тоҷикӣالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ጉዞ ላይ ሰዎች በሚያድሩበት የግመልና የመኝታ ድንኳናቸው ስፍራቸው ውስጥ ባሉበት ወደ ሰዎች በግመል ላይ የምትንጠለጠል ገመድ እንድትቆረጥ የሚያዝ አንድን ሰው ላኩ። ይህም የቀስት ገመድም (ወተር) ይሁን ወይም ከርሱ ውጪ የቃጭልና የጫማ ገመድ የመሳሰሉም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። ይህም የሰው አይን ፈርተው ያስሩት ስለነበር ነው። እንዲቆርጡት የታዘዙበት ምክንያትም ከነርሱ ላይ አንዳችም ነገር ስለማይመልስ ነው። ጥቅምና ጉዳት አጋር በሌለው በአላህ እጅ ብቻ ነውና።فوائد الحديث
የቀስት ገመድና ማንኛውንም ገመድ ጥቅም ያመጣል ወይም ጉዳት ይከላከላል በሚል ማሰር ከሺርክ የሚመደብ ስለሆነ ክልክል ነው።
ከቀስት ገመድ ውጪ ያሉ ገመዶችን ማሰር ለውበት ወይም እንስሳን ለመምራት ወይም በርሱ ለማሰር ከሆነ ችግር የለውም።
መጥፎን በቻሉት መጠን ማውገዝ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ልብን አጋር በሌለው አላህ ላይ ብቻ ማንጠልጠል ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
አላህን በተመላኪነቱ መነጠል