'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች)

'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች)

ዐብደሏህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፡ 'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች) ጠፉ!' ሶስት ጊዜ ደጋገሟት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ያመጡትን ሸሪዓዊ ወሰን ያለ ምንም መመሪያና እውቀት ወሰን ተላልፈው በንግግራቸውም ይሁን በተግባራቸው በእምነታቸውም ይሁን በአለማዊ ጉዳያቸው ፅንፍ የሚረግጡ ሰዎች ያለባቸውን ውርደትና ኪሳራ ተናገሩ።

فوائد الحديث

በየትኛውም ጉዳይ በተለይም በዒባዳና ፃድቃንን በማላቅ ረገድ ወሰን ማለፍና ያላቅም መንጠራራት መከልከሉ፤ ከእንዲህ አይነቱ ነገር መራቁ በየትኛውም ጉዳይ ላይ እንደሚበረታታ፤

በአምልኮም ይሁን በሌላው ጉዳይ ተስተካክሎ የተሟላውን መፈለግ እንደሚገባ፤ ይህም የሚሆነው ሸሪዓውን በመከተል መሆኑ፤

አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ጠንከር ማድረግ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህንኑ እንኳ ሲናገሩ ሶስት ጊዜ ደጋግመው ነውና የተናገሩት።

የእስልምና ገራገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል, አላህን በተመላኪነቱ መነጠል