እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ

እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ

ጁንዱብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመሞታቸው አምስት (ሌሊቶች) በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡- ' እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ እንደያዘው ሁሉ እኔንም ፍፁም ወዳጅ አድርጎ ይዞኛልና። ከኡመቴ ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዝ ብሆን ኖሮ አቡበከርን ነበር ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዘው። አዋጅ! እነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የነብያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር መስገጃ ስፍራ አድርገው ይይዙ ነበር። አዋጅ! መቃብርን መስገጃ ስፍራ አድርጋችሁ አትያዙ! እኔ እየከለከልኳችሁ ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአላህ ዘንድ ያላቸው ደረጃ አሳወቁ፤ ልክ እንደ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም እሳቸውም ላእላይ እርከን የደረሰ ውዴታ መጎናፀፋቸውንም ተናገሩ። ከአሏህ ውጭ ፍፁም ወዳጅ ሊኖራቸው እንደማይችል ገለፁ። ምክንያቱም ልባቸው በአላህ ውዴታ፣ ማላቅና ማወቅ ተሞልቷልና ከአላህ ውጪ ለሳቸው ሌላ ፍፁም ወዳጅ ሊኖራቸው አይችልም። ከፍጡራን ፍፁም ወዳጅ የሚይዙ ቢሆኑ ኖሮ ያ ሰው አቡበከር አስሲዲቅ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ይሆን ነበር። ከዚያም አይሁዶችና ክርስቲያኖች የነቢያቶቻቸውና የፃድቃኖቻቸው መቃብር ከአላህ ውጪ ወደምትመለክ ጣኦታዊ የአምልኮ ስፍራ እስክትለወጥ እንዲሁም መስገጃና ቤተ መቅደሶችን መቃብሮቻቸው ላይ በመገንባት የፈፀሙትን ልክ ያለፈ የውዴታ ድንበር ማለፍ አስጠነቀቁ። አስከትለውም ኡመታቸውም የነሱን አይነት ድርጊት እንዳይፈፅሙ ከለከሉ።

فوائد الحديث

አቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ያላቸውን በላጭነት፤ ከሶሓቦችም ሁሉ በላጩ እርሳቸው መሆናቸውን፤ ከረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በኋላ በርሳቸው የመሪነት ቦታ ለመተካት ይበልጥ የተገቡትም እርሳቸው መሆናቸውን፤

በመቃብር ላይ መስገጃ መገንባት ያለፉት ህዝቦች ከሚፈፅሟቸው ውግዝ ተግባራት መካከል መሆኑ፤

ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል መቃብርን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ፣ በውስጧም ሆነ ወደሷ ዞሮ መስገድ፣ ወይም በላያቸው ላይ መስገጃ ወይም ጉልላት መስራት ክልክል መሆኑ፤

ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል በፃድቃን ላይ ድንበር ከማለፍ መጠንቀቅን፤

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከመሞታቸው አምስት ቀናት ቀደም ብለው ማስጠንቀቃቸው ያስጠነቀቁት ጉዳይ ያለውን አሳሳቢነት እንደሚያሳይ እንረዳለን።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል, የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ