የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል።

የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የጠራውና ከፍ ያለው አላህ በሁሉም ሌሊት የሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ በመውረድ ባሮቹ እንዲለምኑት እንደሚያነሳሳ፤ እርሱ ለለመነው ተቀባይ፤ ለጠየቀው ሰጪ ነውና፤ የሚፈልጉትን እንዲጠይቁት የሚያነሳሳ፤ እርሱ ለአማኝ ባሮቹ መሀሪ ነውና ለወንጀሎቻቸውም ከርሱ ምህረትን እንዲፈልጉ የሚያብረታታቸው መሆኑን ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ገለፁ።

فوائد الحديث

የሌሊቱ የመጨረሻው ሲሶ ትሩፋቱንና በዚህ ወቅት ሶላት መስገድ ፣ ዱዓእ ማድረግና ምህረትን መፈለግ ያለውን ደረጃ እንረዳለን።

አንድ ሰው ይህንን ሐዲሥ በሚሰማበት ጊዜ ዱዓእ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅትን በመሸመት ላይ እጅግ የሚጓጓ ሊሆን ይገባል።

التصنيفات

አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል