إعدادات العرض
ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'
ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ሰዎች የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለጠንቋዮች ጠየቁ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነርሱ 'ምንም አይደሉም።' በማለት መለሱ። እነሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ተናግረው እውነት ይሆናል።' አሉ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ' ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ ไทย 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Hausa دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Soomaali Deutsch Moore Українська Български Wolof Azərbaycan ქართული тоҷикӣالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለወደፊት ስለሚከሰቱ የሩቅ ሚስጥራት ስለሚናገሩ ሰዎች ተጠየቁ። እሳቸውም: ቦታ አትስጡት ፤ ንግግራቸውን አትያዙ፤ ጉዳያቸው አያሳስባችሁ አሉዋቸው። ሶሐቦችም "በእንዲህ ወርና በእንዲህ ቀን" ብለው የሩቅ ሚስጥር ጉዳይ እንደሚከሰት እንደሚናገሩና እንደተናገሩት ገጥሞ መከሰቱን አይነት ንግግራቸው አንዳንድ ጊዜ ተጨባጩን የሚገጥም መሆኑን ተናገሩ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም እንዲህ ብለው መለሱላቸው "ጂኖች ከሰማይ የሚሰሙትን ወሬ በመስረቅ ወደ ጠንቋይ ወዳጆቻቸው አውርደው የሰሙትን ይነግሯቸዋል። ከዚያም ጠንቋዩ ከሰማይ በሰማው ላይ መቶ ውሸት ይጨምርበታል።"فوائد الحديث
ጠንቋዮችን ማመን መከልከሉን ፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ቢናገሩ እንኳ የሚናገሩት ነገር ውሸትና ቅጥፈት መሆኑን እንረዳለን።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመላካቸው ምክንያት ከተወርዋሪ ኮኮብ አምልጦ ወሬ የሰረቀ ጂን ካልሆነ በቀር ሰይጣናት ከወሕይም ይሁን ሌላ እንዳይሰሙ ሰማይ ተጠብቃለች።
ጂኖች ከሰው የሆነ ወዳጅ እንደሚይዙ እንረዳለን።