إعدادات العرض
አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።
አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።
ሙዓዝ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ : ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኋላ ዑፈይር የሚባለው አህያ ላይ ተፈናጥጬ ሳለው "ሙዓዝ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅ፤ ባሮችስ አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ ታውቃለህን? " አሉ። "አላህና መልክተኛው ይወቁ !" አልኩኝ። እሳቸውም "አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።" አሉ። "የአላህ መልክተኛ ሆይ ሰዎችን ላበስራቸውን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አታበስራቸው (በዚህ ስራ ላይ ብቻ) ይደገፋሉ (ይሳነፋሉ)። " አሉ።
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Kurdî Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Oromoo Wolof Soomaali Tagalog Français Azərbaycan Українська Português bm தமிழ் ქართული Deutsch Македонски فارسی Magyar Русский 中文 km Malagasyالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅና ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ አብራሩ። አላህ ባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ እሱን ብቻ ሊያመልኩና በሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ባሮች በአላህ ላይ ያላቸው ሀቅ ደግሞ እነዚያ በሱ ላይ አንዳችንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ያመለኩትን ላይቀጣ ነው። ቀጥሎ ሙዓዝ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎች በደስታ እንዲበሰሩ በዚህ የላቀ የአላህ ትሩፋት ላበስራቸውን?" አለ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሷ ላይ መደገፋቸውን ፈርተው እንዳያበስራቸው ከለከሉት።فوائد الحديث
አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገው ሐቅ መገለፁ፤ እሱም፥ ሊያመልኩትና በሱ ላይም ምንንም ላያጋሩ መሆኑ።
አላህ በችሮታውና በፀጋው በነፍሱ ላይ ግዴታ ያደረገው ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ መገለፁ፤ እሱም ጀነት ሊያስገባቸውና ላይቀጣቸው ነው።
እዚህ ሐዲሥ ውስጥ አላህ ላይ አንዳችንም የማያጋሩ የተውሒድ ሰዎች መመለሻቸው ጀነት መሆኑን የሚገልፅ ትልቅ ብስራት አለ።
ሙዓዝ ዕውቀት የመደበቅ ወንጀል ውስጥ መውደቅ ፈርተው፥ ይህን ሐዲሥ የተናገሩት ከመሞታቸው በፊት (ወደ ሞት አፋፍ ሲቃረቡ) ነው።
አንዳንድ ሐዲሦችን ከፊል ሰዎች ትርጉሙን በአግባቡ አይረዱትም ተብሎ ከተሰጋ አለመናገር እንደሚገባ ያስገነዝበናል። ይህ የማንነግራቸው ሐዲሥ ግን በሐዲሡ ስር ተግባርን የሚያዝና ሸሪዐዊ የቅጣት ብይኖችን የሚያስቀምጥ ሐዲሥ ካልሆነ ነው።
የተውሒድ ሰዎች ሆነው ወንጀል የሰሩ በአላህ ፍላጎት ስር ናቸው። ከፈለገ ይቀጣቸዋል። ከፈለገም ይምራቸዋል። ከዛም ግን መመለሻቸው ወደ ጀነት ነው።