إعدادات العرض
1- አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም።
2- አላህ በእርሱ ላይ እሳትን እርም ቢያደርግ እንጂ አንድም በእውነተኛ ልቡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን የሚመሰክር የለም።
3- አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች በአላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።
4- በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።
5- የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
6- የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንጀል ትንሽም ሆነ ትልቅ የሰራሁት ቢሆን እንጂ አልተውኩትም! " አለ። እርሳቸውም "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?
7- የሥራ ዓይነቶች ስድስት ሲሆኑ፤ የሰው ዓይነቶች ደግሞ አራት ናቸው። (የሥራ ዓይነቶች) ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉ፣ አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ፣ በአስር ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ፣ በሰባት መቶ ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ ናቸው።
8- ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ