የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንጀል ትንሽም ሆነ ትልቅ የሰራሁት ቢሆን እንጂ አልተውኩትም! " አለ። እርሳቸውም "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ…

የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንጀል ትንሽም ሆነ ትልቅ የሰራሁት ቢሆን እንጂ አልተውኩትም! " አለ። እርሳቸውም "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?

አነስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት " የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንጀል ትንሽም ሆነ ትልቅ የሰራሁት ቢሆን እንጂ አልተውኩትም! " አለ። እርሳቸውም "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?" በማለት ሶስት ጊዜ ጠየቁት። እርሱም "አዎን" አለ። እሳቸውም "ይህ ምስክርህ በነዛ ወንጀሎችህ ላይ ያልፋሉ (ወንጀሎችህን ያብሳቸዋል)" አሉት።

[ሶሒሕ ነው።] [Abu Ya‘laa]

الشرح

አንድ ሰው ወደ ነቢዩየአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሁሉንም ዓይነት ወንጀሎችና ኃጢኣቶች ሰርቻለሁ፤ ትንሽም ሆነ ትልቅ ወንጀል ከመስራት አልተቆጠብኩም፤ ምህረት ይደረግልኝ ይሆን?" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሱ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?" አሉት። ሶስት ጊዜ ደጋግመው ጠየቁት። እርሱም፦ "አዎን እመሰክራለሁ" በማለት መለሰላቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሁለቱ የምስክር ቃላቶች ትሩፋትና ወንጀል የማስማር አቅማቸው እንደሚማር ነገሩት። ተውበት ያለፈውን ወንጀል ያብሳልና።

فوائد الحديث

የሁለቱ ምስክር ቃላት ታላቅነትና እውነተኛ በሆነ ልቡም የተናገራት ጊዜ ወንጀሎች ላይ የሚኖራት የበላይነት።

እስልምና ያለፈን ወንጀል የሚያብስ (የሚያስምር) መሆኑን።

እውነተኛ ተውበት (ጸጸት) ያለፈን ወንጀል የምታብስ መሆኑን።

በማስተማር ሂደት ውስጥ መደጋገም ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ፈለግ መካከል መሆኑን።

የሁለቱ ምስክር ቃላቶች ትሩፋት፥ እሳት ውስጥ ከመዘውተር ለመዳን ሰበብ መሆናቸው።

التصنيفات

የተውሒድ ትሩፋቶች