إعدادات العرض
የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል። በሱ ላይም ዘጠና ዘጠኝ መዝገብ ይዘረጋበታል፤ ሁሉም መዝገብ ዓይን የሚያየውን ርቀት አምሳያ ያካልላል። ከዚያም "ከዚህ ውስጥ አንዳችም ቢሆን (አልሰራሁትም ብለህ) የምታስተባብለው አለን? ስራን ጠባቂ ጸሐፊዎቼ በድለውሀልን? " ብሎ ይጠይቀዋል። "ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። "ተቀባይነት ያለው ምክንያትስ \ ማስተባብያስ አለህን?" ይለዋል። " ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። አላህም "እንዴታ! እኛ ዘንድ አንድ መልካም ሥራ አለችህ። እነሆ ዛሬ ባንተ ላይ ምንም በደል የለም።" ይለዋል። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ (ላኢላሀ ኢለ'ላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ) የሚልን ጽሑፍ የያዘች አንድ ካርድ ትወጣለች። አላህ "ሚዛንህ ላይ ተገኝ!" ይለዋል። እሱም "ጌታዬ ሆይ ይህቺ ካርድ ከነዚህ ሁሉ መዝገቦች ጋር (ስትነፃፀር) ምን ዋጋ አላት? " ይላል። አላህም "አንተ አትበደልም።" ይለዋል። መዝገቦቹ በአንድ በኩል ካርዷ በአንድ በኩል ለሚዛን ሲቀመጡ ካርዷ መዝገቦቹን ጠቅልላ ሚዛን ደፋች። ከአላህ ስም ጋር ምንም ሚዛን ሊደፋ አይችልም።
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Kurdî Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Oromoo Wolof Soomaali Tagalog Français Azərbaycan Українська Português bm தமிழ் Deutsch ქართული Македонски فارسی Magyar Русский 中文الشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች መካከል ከህዝባቸው አንድ ሰው እንደሚመርጥ ተናገሩ ፤ ሊመረመር ይጠራል፤ በሱ ላይም በዱንያ ይሰራቸው የነበሩትን የወንጀል ተግባራት የያዘ ዘጠና ዘጠኝ መዝገብ ይቀርባል ፤ የእያንዳንዱ መዝገብ ርዝመትም ዓይን የሚያየውን ርቀት ያካልላል። ከዚያም የተከበረውና የላቀው አላህ ለዚህ ሰውዬ፦ "በነዚህ መዝገቦች ውስጥ ከተጻፉት አንድም ብትሆን የምታስተባብለው አለህን?" ይለዋል። "ሥራህን ጸሐፊና ተጠባባቂ የሆኑት መላእክቶቼ በድለውሀልን?" ይለዋል ሰውዬውም "ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። የተከበረውና የላቀው አላህም "ላንተ በዱንያ አስቀድመህ ለሠራሀቸው ወንጀሎች ተቀባይነት የሚያገኝ ምክንያት አለህን?" በመርሳት፣ በመሳሳት ወይ ባለማወቅ ነው ብለህ ምክንያት የምታቀርብበት ይለዋል። ሰውዬውም፦ "ጌታዬ ሆይ በፍፁም ለኔ ምንም ምክንያት የለኝም።" ይላል። የተከበረውና የላቀው አላህም "እንዴታ! እኛ ዘንድ አንድ መልካም ሥራ አለችህ። እነሆ ዛሬ ባንተ ላይ ምንም በደል የለም" ይላል። ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ (አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለላህ ወ አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ ) የሚል የተፃፈባት አንድ ካርድ ትወጣለች።" የተከበረውና የላቀው አላህ ለዚህ ሰውዬ፦ "ሚዛንህ ላይ ተገኝ!" ይለዋል። ሰውዬውም በመደነቅ "ጌታዬ ሆይ ይህቺ ካርድ ከነዚህ መዝገቦች ጋር (ስትነፃፀር) ምን ትመዝናለች?" ይላል። የተከበረውና የላቀው አላህም፦ "ባንተ ላይ ምንም በደል አይደርስብህም" አለው። ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ " መዝገቦቹ በአንድ በኩል ካርዷ በአንድ በኩል ትቀመጣለች። መዝገቦቹ ያሉበት ሚዛን ስትቀል ካርዷ ያለችበት ሚዛን ደግሞ የከበደችና ሚዛን የደፋች ሆነች። በዚህም አላህ ማረው።فوائد الحديث
የተውሒድ ቃል ታላቅነት፥ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ (ሸሀደቱ አላ ኢላሀ ኢለ'ላህ) የሚለው ቃል ሚዛንን የሚከብድ መሆኑን።
ላ ኢላሀ ኢለላህን በምላስ ብቻ መናገር በቂ አይደለም። የግድ ትርጉሙን ማወቅና የሚያስገነዝበውን ተግባር መስራትም አስፈላጊ መሆኑን።
ኢኽላስና የተውሒድ ኃይል ወንጀልን ለማስማር (ለማሰረይ) ምክንያት ናቸው።
ኢማን ቀልቦች ውስጥ በሚኖረው የኢኽላስ መጠን ልክ ይበላለጣል። አንዳንድ ሰው ይህንን የተውሒድ ቃል ቢናገርም ነገር ግን በወንጀሉ ልክ ይቀጣል።