አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም።

አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም።

ከአቡ ሰዒድና አቡ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ሙስሊምን ከበሽታዎች ፣ ከጭንቀቶች፣ ከሀዘኖች፣ ከችግሮች፣ ከመከራዎች፣ ከመአቶች እንዲሁም ከፍርሀትና ረሀብ ቢደርስበት አንዲት እሾህ እንኳ ብትወጋውና ብታሳምመው ለርሱ ወንጀሎቹን ማስማሪያና ኃጢአቶቹን ማስሰረያ እንደሚሆንለት የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።

فوائد الحديث

አላህ በአማኝ ባሮቹ ላይ በሚደርስባቸው ትንሽ ጉዳት ምክንያት ወንጀሎችን መማሩ በአማኝ ባሮቹ ላይ ያለው ችሮታና እዝነቱን ይገልፃል።

አንድ ሙስሊም የሚደርስበት ችግር ለደረጃው ከፍታና ለወንጀሉ መማሪያ እንዲሆንለት አላህ ዘንድ የሚያገኘውን ምንዳ በማሰብ፤ በትንሹም ሆነ በትልቁ መከራ ሁሉ ሊታገስ ይገባዋል።

التصنيفات

የተውሒድ ትሩፋቶች