ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ

ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአጎታቸው እንዲህ አሏቸው፦ " ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ" አቡ ጣሊብም "የቁረይሾች ማነወር ባልነበር "ለመስለም ያነሳሳው የሞት ፍራቻ ነው" ይላሉ ብዬ ባልሰጋ (እሰልም ነበር)" (ይህ ስጋት ባልነበር) ላ ኢላሀ ኢለላህ በማለት ደስታን አሰርፅልህ ነበር።" አላቸው። አላህም ይህን አንቀፅ አወረደ {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።} [አልቀሶስ: 56]

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አጎታቸው አቡ ጣሊብ ጣእረ ሞት ላይ ሳሉ ላኢላሀ ኢለላህን እንዲናገር ፈለጉ። ይህም የትንሳኤ ቀን በሷ ምክንያት ሊያማልዱትና በእስልምናው ሊመሰክሩለት ብለው ነው። አቡ ጧሊብ ግን ቁረይሾች እንዳይሰድቧቸው ፈርተውና "እርሱ የሰለመው ሞትና ደካማነትን በመፍራቱ ምክንያት ነው!" እንዳይባሉ በመስጋት የምስክርነት ቃሏን መናገር እምቢ አሉ። ለነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ይህ ስጋቴ ባልነበር የምስክር ቃሏን በመናገር በልብዎ ውስጥ ደስታን አስገባም ነበር እስኪደሰቱ ድረስም ምኞቶን አሳካ ነበር" አሏቸው። አላህም የፈለገውን ሰው እርሱ ብቻ እንጂ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኢስላምን በሰው ቀልብ ውስጥ በማስረፅ መምራት እንደማይችሉ የሚጠቁም አንቀፅ አወረደ። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፍጡራንን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በመጠቆም ፣ በማብራራት፣ በማቅናትና በመጣራት ነው የሚመሩት።

فوائد الحديث

የሰዎችን ወሬ በመፍራት ሐቅ አይተውም።

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጠቆምና የማቅናት መምራት እንጂ የሚችሉት ልብ ውስጥ የማስረፅ መምራት እንደማይችሉ እንረዳለን።

ወደ ኢስላም ለመጥራት ብሎ የታመመን ከሀዲ መዘየር በኢስላም የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በማንኛውም ሁኔታዎች ወደ አላህ በመጥራት ላይ የነበራቸውን ጉጉት ተረድተናል።

التصنيفات

በአላህ ፍርድና ውሳኔ ማመን, ኢስላም, የተውሒድ ትሩፋቶች