إعدادات العرض
አላህ ለኔ ከኡመቴ ላይ በመሳሳት፣ በመርሳትና በመገደድ ለሚያደርጉት ነገር ይቅር ብሏቸዋል።
አላህ ለኔ ከኡመቴ ላይ በመሳሳት፣ በመርሳትና በመገደድ ለሚያደርጉት ነገር ይቅር ብሏቸዋል።
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "አላህ ለኔ ከኡመቴ ላይ በመሳሳት፣ በመርሳትና በመገደድ ለሚያደርጉት ነገር ይቅር ብሏቸዋል።"»
[قال النووي: حديث حسن] [رواه ابن ماجه والبيهقي وغيرهما]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල دری অসমীয়া پښتو O‘zbek Tiếng Việt Македонски ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ తెలుగు ไทย Moore Magyar Azərbaycan ქართული ಕನ್ನಡ Yorùbá ગુજરાતી Українська Shqip Кыргызча Српски Kinyarwanda тоҷикӣ Wolof Čeština தமிழ் नेपाली മലയാളം kmr ms Deutsch Lietuviųالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ ለኡመታቸው በሶስት ሁኔታዎች ላይ እያሉ የሰሩትን ወንጀል ይቅር እንዳለ ተናገሩ:- የመጀመሪያው: በስህተት: ማለትም ሆነ ብለው ሳይሆን የሰሩት ወንጀል ማለት ነው። ይህም ማለት አንድ ሙስሊም በድርጊቱ አንዳችን ነገር ማሰቡና ድርጊቱ ግን ካሰበው ውጪ ሆኖ መገኘቱ ነው። ሁለተኛው: በመርሳት: ይህም ማለት አንድ ሙስሊም አንድን ነገር ለመስራት ያስባል። ነገር ግን ድርጊቱን ለመስራት ባሰበበት ወቅት ይረሳዋል። በዚህም ወንጀል አይኖርበትም። ሶስተኛው: በመገደድ ነው። አንድ ባሪያ መስራት ሳይፈልግና አስገዳጁንም አካል መከላከል በማይችልበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ተገዶ አንድን ድርጊት ሊሰራ ይችላል። በዚህ ጊዜ በርሱ ላይ ወንጀል ወይም ጣጣ አይኖርበትም። የሐዲሡ ሃሳብ ግን በባሪያና በጌታው መካከል የተከለከለን በመስራት ላይ መርሳትን የሚመለከት ነው። ትእዛዝን ረስቶ ቢተው ግን ትእዛዙ አይነሳለትም። እነዚህን ነገሮች ተከትሎ የተከሰተ ወሰን አላፊነት ካለ የፍጡርም ሐቅ አይነሳለትም። በስህተት የገደለ ሰው ለምሳሌ በርሱ ላይ ጉማ ይኖርበታል። ወይም በስህተት መኪና ቢያጠፋ በርሱ ላይ መኪናውን መክፈል አለበት።فوائد الحديث
የአላህ ዓዘ ወጀል እዝነት ስፋትና ለባሮቹ መራራቱን እንረዳለን። ይህም ባሮቹ ወንጀልን በነዚህ ሶስት ሁኔታዎች ላይ ሆነው ቢሰሩ ወንጀልነቱን ከነርሱ ላይ ማንሳቱ ነው።
አላህ ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እና ለኡመታቸው የዋለውን ችሮታ ሰፊነቱን እንረዳለን።
ወንጀልነቱ ይነሳል ማለት ብይኑ ወይም ካሳው ይነሳለታል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ዉዱእን የረሳና ዉዱእ ያለው መስሎት የሰገደ ሰው በዚህ ወንጀል አይኖርበትም። ነገር ግን ዉዱእ ማድረግና ሶላቱን መድገም ይኖርበታል።
በመገደድ ምክንያት ወንጀልነቱ እንዲነሳ የግድ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች አሉ።ለምሳሌ: አስገዳጁ የዛተውን ነገር በተገዳጁ ላይ ለመፈፀም አቅም ያለው መሆን አለበት።
التصنيفات
በአላህ ማመን