إعدادات العرض
'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።
'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።
ከዑቅባህ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው፦ "ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተወሰኑ ሰዎች መጡ። ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋቡና ከአንዱ ጋር ቃልኪዳን ከመጋባት ተቆጠቡ። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋብተው ይህንን ለምን ተዉ?' አሉ። እርሳቸውም 'እርሱ ላይ ሒርዝ ስላለ ነው።' አሉ። (ይህንን ሲሰማ) እጁን አስገባና ቆረጠው። እርሳቸውም ቃልኪዳን ተጋቡትና 'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።"
[ሐሰን ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy Čeština नेपाली Oromoo Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย Српски മലയാളം Kinyarwanda Română ಕನ್ನಡ Lietuviųالشرح
የተወሰኑ ጭፍሮች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። ብዛታቸውም አስር ነበሩ። ከነርሱ መካከል ከዘጠኙ ጋር በኢስላም ላይና እርሳቸውን በመከተል ላይ ቃል ተጋቡና ከአስረኛው ጋር ቃልኪዳን ሳይጋቡ ቀሩ። የዚህን ምክንያት የተጠየቁ ጊዜም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: እርሱ ላይ ሒርዝ አለበት። (ሒርዝ) ማለት፦ ዓይንን ወይም ጉዳትን ለመከላከል ከጨሌና ከሌላም ነገር የሚሰራ የሚታሰር ወይም የሚንጠለጠል ነው። ሰውዬውም ወደ ሒርዙ ስፍራ እጁን ከቶ በመቁረጥ ከሒርዙ ጠራ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዚህ ጊዜ ቃልኪዳን ተጋቡት። ከሒርዝ ለማስጠንቀቅና ብይኗን ለመግለፅም እንዲህ አሉ: "ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል።"فوائد الحديث
ከአላህ ውጪ በሆነ ላይ የተመካን ሰው አላህ ጉዳዩን ካሰበው በተቃራኒ ያደርግበታል።
ጉዳትንና ዐይንን ለመከላከል ሒርዝ ማንጠልጠል ሰበብ ይሆናል ብሎ ማመን ትንሹ ሺርክ ነው። በራሷ ትጠቅማለች ብሎ ካመነ ግን ትልቁ ሺርክ ነው የሚሆነው።
التصنيفات
አላህን በተመላኪነቱ መነጠል