'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'

'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'

ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መቃብሮች ላይ ከመቀመጥ ከለከሉ። ይህም ወደ መቃብሮች ከመስገድ እንደከለከሉት ነው። ቀብሩ ወደ ሰጋጁ ቂብላ አቅጣጫ መሆኑን ይመስል ማለት ነው። ይህም የተከለከለው ወደ ሺርክ ከሚያዳርሱ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ነው።

فوائد الحديث

በሐዲስ እንደተረጋገጠው የጀናዛ ሶላት ካልሆነ በቀር በመቃብር ስፍራ ወይም በመቃብሮች መካከል ወይም ወደ መቃብር ዙሮ መስገድ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

ወደ መቃብር መስገድ የተከለከለው የሺርክን መዳረሻዎች ለመዝጋት ነው።

ኢስላም በመቃብር ወሰን ማለፍንም መቃብር ማዋረድንም ከልክሏል። ወሰን ማለፍም ማሳነስም የለምና።

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "የሙትን አጥንት መስበር በህይወት እንደመስበር ነው።" ስላሉ የሙስሊም ክብር ከሞተ በኋላም ዘላቂ ነው።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል, አላህን በተመላኪነቱ መነጠል, የሶላት መስፈርቶች, የሶላት መስፈርቶች