إعدادات العرض
አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጻፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት…
አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጻፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም አልፎ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎች ይጻፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጻፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ አላህ እንዲህ አለ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጻፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም አልፎ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎች ይጻፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጻፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français Tiếng Việt Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Русский Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە සිංහල ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan bm ქართული Македонски Malagasyالشرح
መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን እንደወሰነ ከዚያም ለሚፅፉት ሁለት መላእክቶች እንዴት እንደሚፅፉት እንዳብራራ ገለፁ። መልካምን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ሰው ባይሰራትም እንኳ ለሱ አንድ ምንዳ ትፃፍለታለች። ከሰራት ደግሞ በስራዋ አምሳያ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ከዚያም አልፎ እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ ትባዛለች። ይህ የምንዳ ጭማሪው ቀልቡ ውስጥ ባለው ኢኽላስ፣ በጥቅሙ ወደ ሌሎች ተሻጋሪነትና በመሳሰሉት ልክ ተንተርሶ ነው ። ኃጢዐትን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ከዚያም ለአላህ ብሎ ሳይሰራት የተዋት ሰው ለሱ አንድ ምንዳ ይጻፍለታል። ወደዛች ኃጢዐት የሚያዳርሱ መንስኤዎችን ካለመፈፀም ጋር በሌላ ነገር በመጠመዱ ሳቢያ ከተዋት ምንም ነገር አይፃፍለትም። ኃጢዐቱን መስራት ስለተሳነው ከተወ ደግሞ በሱ ላይ ያለመው ትፃፍበታለች። ከሰራት ደግሞ አንዲት ሀጢዐት ትፃፍበታለች።فوائد الحديث
መልካም ስራዎችን ማነባበሩ፣ እሱ ዘንድ መፃፉና ሀጢዐቶችን ስንሰራ ደግሞ አለማነባበሩ አላህ ለዚህ ኡመት የዋለውን ትልቅ ችሮታ ያብራራል።
በስራዎች ላይ የኒያ አስፈላጊነትና ተፅእኖን ተረድተናል።
መልካምን ሊሰራ አስቦ ላልሰራ ሰው አላህ ለሱ ምንዳ መፃፉ የአላህን ችሮታ፣ እዝነትና መልካምነትን ያስረዳል።
التصنيفات
አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል