የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው…

የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'

ከአቢል ሀያጅ አልአሰዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ለኔ እንዲህ አለኝ: 'የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦቻቸውን "ምስልን" (እሱም አካል ይኑረውም አይኑረው የነፍስ ያለው ነገር ምስል ነው።) ያስወገዱት ወይም ያወደሙት ቢሆን እንጂ እንዳይተዉት ይልኩ ነበር። ከፍ ያለ ቀብርንም ከምድር ጋር እኩል ያደረጉትና በላዩ ላይ የተገነባውንም ያወደሙ ወይም ከመሬት ብዙም ከፍ ሳይል አንድ ስንዝር ብቻ ከፍ በማድረግ ያስተካከሉት ቢሆን እንጂ እንዳይተዉት ይልኩ ነበር።

فوائد الحديث

ነፍስ ያላቸው ነገራቶችን ምስል ማድረግ ወደ ሺርክ ስለሚያዳርስ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

ስልጣን ወይም አቅም ላለው ሰው መጥፎን ነገር በእጅ ማስወገዱ መደንገጉን ፤

ስዕላ ስእሎች፣ ቅርፃ ቅርፆችና ቀብር ላይ መገንባትን የመሳሰሉ ወደ ጃሂሊያ ዘመን ፈለጎች የሚጠቁሙ ነገሮችን ሁሉ በማስወገድ ላይ የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ጉጉት እንረዳለን።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል