የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'

የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የቂያማ ቀን በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተባሉ። የአላህ መልዕክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፡- 'አቡ ሁረይራ ሆይ! ባንተ ላይ ካየሁት የሐዲሥ ጉጉት አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚቀድምህ አይኖርም ብዬ አስቤ ነበር። የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን በምልጃቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ እድለኛ የሚሆኑት "ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት" ማለትም ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው እንደሌለ አምነው ከሽርክ ይሁን ከይዩልኝና ይስሙልኝም ጥርት ያሉት መሆናቸውን እየነገሩን ነው።

فوائد الحديث

ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አኼራ ላይ ሸፋዓ እንደሚያደርጉና ሸፋዓቸውም ተውሒድ ላላቸው ሰዎች መሆኑን ያፀድቃል፤

የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሸፋዓ ተውሒድ ላይ እያለ (በኃጢዓቱ ምክንያት) ጀሀነም የተፈረደበትን ወደ ጀሀነም እንዳይገባ፤ ከገባ ደግሞ እንዲወጣ የሚያደርጉት ምልጃ ነው፤

ለአላህ ጥርት ተደርጋ የተባለች የተውሒድ ቃል ያላት ትሩፋትና የምታሳድረው ከፍተኛ ፋና፤

የተውሒድ ቃል የሚረጋገጠው ትርጉሟን በማወቅና በምታስፈርደው ተግባራዊ በማድረግ ነው፤

አቢ ሁረይራ ያላቸውን ደረጃና በዕውቀት ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል