በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።

በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።

ከዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያለው: የተውሒድን ቃል ትርጉሙን አውቆ የሚያስፈርደውንም በመስራት የተናገረ ሰው፤ እንዲሁም በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባርነትና መልክተኝነት የመሰከረ፤ የዒሳን ባርነትና መልክተኝነት ያመነ፤ አላህ ዒሳን "ሁን" በሚለው ቃሉ እንደፈጠራቸውና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ ነፍስ እንደሆኑም የመሰከረ፤ አይሁዶች ወደርሷ ካስጠጉት ዘለፋም እናቱን መርየምን ያጠራ፤ መኖራቸውንና የአላህ ፀጋና ቅጣቱ መሆናቸውን ከማመን ጋር ጀነትም እውነት መሆኑን፣ እሳትም እውነት መሆናቸውን ያመነ ሰው በአምልኮዎች ላይ ያጓደለና ወንጀሎችም ያሉበት ቢሆን እንኳ በዚህ እምነት ላይ ከሞተ መመለሻው ወደ ጀነት ነው።

فوائد الحديث

ከፍ ያለው አላህ የመርየም ልጅ ዒሳን "ሁን" በሚለው ቃሉ ብቻ ያለ አባት ነው የፈጠራቸው።

ዒሳና ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈንና) የአላህ ባሪያዎችና መልዕክተኛዎች በመሆናቸው የማይስተባበሉ መልክተኞችና የማይመለኩ ባሪያዎች መሆናቸውን እንረዳለን።

የተውሒድን ትሩፋትና ወንጀሎችን እንደሚያስምር እንረዳለን። ተውሒድን የያዘ ሰውም ከፊል ወንጀል ላይ ቢወድቅ እንኳ መመለሻው ጀነት ነው።

التصنيفات

በአላህ ማመን, በመጨረሻው ቀን ማመን, የጀነትና እሳት ባህሪዎች