ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እኔ የአሏህ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህም የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ።'

ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እኔ የአሏህ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህም የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ።'

ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡ "ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እኔ የአሏህ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህም የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ክርስቲያኖች ዒሳ ዓለይሂ ሰላምን በተመለከተ ወሰን እንዳለፉት ሁሉ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ህዝባቸው እሳቸውን በማሞገስ በኩል፣ በአላህ ባህሪያትና ልዩ ድርጊቶቹ እሳቸውን በመግለፅ፣ የሩቅ እውቀትን እንደሚያውቁ በመሞገት፣ ወይም ከአሏህ ጋር እሳቸውን በመማፀንና በመሳሰሉት መልኩ ወሰን እንዳይታለፍባቸው አስጠነቀቁ። ከዚያም ከአሏህ ባርያዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን ገልፀው፤ እሳቸውን "የአሏህ ባርያውና መልዕክተኛው" ብለን እንድንገልፃቸው አሳሰቡ።

فوائد الحديث

ወደ ሽርክ የሚያደርስ በመሆኑ በማላቅ እና በማወደስ ረገድ ሸሪዓ የደነገገውን ገደብ ከማለፍ መጠንቀቅ እንደሚገባ፤

ይህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ያስጠነቀቁት ነገር በእውነቱ በዚህ ኡማ ተከስቷል። ይህም የተወሰኑት ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ፣ ከፊሎች የነቢዩ ﷺየአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቤተሰቦች ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ወልዮች ላይ ይህ ያስጠነቀቁትን ነገር በመፈፀም ሽርክ ላይ ወድቀዋል።

የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የአሏህ ባሪያው ናቸው እንጂ ከአምላክ መለያዎች መካከል የትኛውም እንደማይገባቸው ለመጠቆም ራሳቸው የአላህ ባሪያ መሆናቸውን ገለፁ።

ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከአሏህ የተላኩ መልዕክተኛው በመሆናቸው ሊያምኗቸውና ሊከተሏቸው እንደሚገባ ለመጠቆም ራሳቸውን የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውንም ገለፁ።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል