إعدادات العرض
አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል
አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
ar en my sv cs gu yo nl ur es id ug bn tr bs si hi vi ha ml te sw ps as sq prs el bg ff kn ky lt or ro rw sr tg uz ne mos ku wo so fr tl az uk bm ta de ka pt mk hu fa ru zh km mg omالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአማኞች ላይ የዋለውን ትልቅ ችሮታና ከከሀዲያን ጋር ያለውን ፍትሀዊነት ያብራራሉ። አማኝ የሆነ ሰው የመልካም ሥራው ምንዳ ምንም አትጎድልም። በአኺራ ከሚደለብለት (ከሚከማችለት) ምንዳ በተጨማሪ በዱንያም በአምልኮው ምክንያት መልካምን ይሰጠዋል። ይህ ካልሆነ እንኳ ሁሉም ምንዳው ለሱ አኺራ ላይ ይጠበቅለታል። ካፊር ግን ለሠራው መልካም ሥራ የሚመነዳው በዱንያ አላህ በሚሰጠው መልካም ነገር ነው። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ ምንም የሚመነዳው ክፍያ አይኖረውም። ምክንያቱም በመልካም ሥራ በሁለቱም ዓለም ለመጠቀም የግድ ባለቤቱ አማኝ መሆን ይጠበቅበታል።فوائد الحديث
በክህደት ላይ የሞተ ሰው ምንም ተግባር አይጠቅመውም።