إعدادات العرض
በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።
በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።
ከእናትችን ዓኢሻና ዐብደላህ ቢን ዓባስ - (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የሞት መልዐክ በአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የወረደ ጊዜ ፊታቸው ላይ ጨርቃቸውን ጣል ማድረግ ጀመሩ ፤ ሲያፍናቸው ደግሞ ይገልጧት ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ 'በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።' አሉ፤ ከሰሩት ስራ እያስጠነቀቁ። '"
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog বাংলা Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ Русский Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە ไทย دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Moore Azərbaycan ქართული Magyarالشرح
እናታችን ዓኢሻና ኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሞት የቀረባቸው ጊዜ የጨርቅ ቁራጭ ፊታቸው ላይ ጣል ያደርጉ እንደነበርና በሞት ስካር ሳቢያ ለመተንፈስ ያስቸገራቸው ጊዜም ከፊታቸው ያስወግዱት እንደነበር ነገረችን። በዚህ ከባድ ሁኔታ ላይ እያሉ አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን እንደረገመ፤ ከእዝነቱም እንዳራቀ፤ ይህም በነቢያቶቻቸው መቃብር ላይ መስገጃ በመገንባታቸው ምክንያት መሆኑን ነገረችን። የጉዳዩ አደገኛነት ከባድ ባልነበር በእንደዚ አይነት ሁኔታ ላይ ሆነው አይጠቅሱትም ነበር። ስለዚህም ይህ የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ድርጊት እንዲሁም በአላህ ላይ ወደ ማጋራት የሚያዳርስ ነውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መሰል ድርጊቶች ላይ ከነርሱ ጋር መመሳሰልን ከለከሉ።فوائد الحديث
የነቢያቶችንና ደጋጎችን መቃብር ለአላህ የሚሰገድበት መስገጃ አድርጎ መያዝ ወደ ሺርክ የሚያዳርስ ስለሆነ መከልከሉን እንረዳለን።
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተውሒድ ላይ ያላቸው ትኩረትና ጥንቃቄ የበረታ መሆኑንና መቃብርን ማላቅም ወደ ሺርክ ስለሚያዳርስ መስጋታቸውን እንረዳለን።
አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን መርገም እንዲሁም ቀብር ላይ በመገንባትና መቃብርን መስገጃ አድርጎ በመያዝ የነርሱን ድርጊት አምሳያ የሰራን ሰውም መርገም እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
በመቃብር ላይ መገንባት የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ሱና መሆኑንና ሐዲሡ ከነርሱ ጋር መመሳሰልንም ይከለክላል።
መስገጃ ባይገነባበት እንኳ እርሱ ዘንድ መስገድና ወደርሱ ዙሮ መስገድ መቃብርን መስገጃ አድርጎ መያዝ ውስጥ ይካተታል።
التصنيفات
አላህን በተመላኪነቱ መነጠል