إعدادات العرض
እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'
እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'
አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Akan Azərbaycan Български Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy नेपाली or Română Kinyarwanda тоҷикӣ O‘zbek Moore Wolof Oromoo bm Українська rn km Српски ქართული Македонски Русскийالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን እየነገሩን ነው፡- አጋርን ከመፈለግ ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃው አሏህ ነው። እርሱም ከምንም የተብቃቃ ራሱን የቻለ ነው። አንድ ሰው መልካም ነገርን ሲያደርግ ለአላህም ለሌሎችም ብሎ ቢያደርገው አላህ ይህንን ስራውን ይተውለታል፤ አይቀበለውም፤ ወደራሱ ይመልስለታል። ስለዚህም ጥራት የተገባው አሏህ ጥርት ባለ መልኩ ለርሱ ተብሎ የተሰራውን መልካም ስራ ካልሆነ በቀር ሌላን ስራ ስለማይቀበል ኢኽላስን ለርሱ ማድረግ ግዴታ ነው።فوائد الحديث
ሽርክ መልካም ስራዎች ተቀባይነት እንዳያገኙ ግርዶ ስለሆነ በሁሉም መልኩ መጠንቀቅን፤
ስራን ለአሏህ ጥርት በማድረግ ላይ ስለሚያግዝ የአሏህን ሙሉ ተብቃቂነትና ታላቅነት ማስተዋል እንደሚያስፈልግ እንረዳለን።