إعدادات العرض
አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል።…
አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog Tiếng Việt Hausa Kurdî Português සිංහල অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી Nederlands پښتو नेपाली ไทย മലയാളം Кыргызча Română Malagasy Svenska తెలుగు Српскиالشرح
ነቢዩ ((የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለጀነት ነዋሪዎች በውስጧ እያሉ እንዲህ እንደሚል ነገሩን: "የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!" እነርሱም "ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል" በማለት ለርሱ ይመልሳሉ። እርሱም ለነርሱ: ተደሰታችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: አዎን ተደስተናል። ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው? ይላሉ። አላህም: ከዚህ የተሻለ ነገር ልስጣችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ነገር ምን አለና? ይላሉ። እርሱም: ዘውታሪ የሆነውን ውዴታዬን አሰፍንባችኋለሁ። ከዚህ በኋላ በናንተ ላይ መቼም አልቆጣም። ይላቸዋል።فوائد الحديث
አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ ከጀነት ነዋሪዎች ጋር እንደሚያወራ እንረዳለን።
የጀነት ነዋሪዎች አላህ ከነርሱ እንደሚወድላቸው፤ በነርሱ ላይ ውዴታው እንደሚሰፍንና በነርሱ ላይ መቼም እንደማይቆጣ በአላህ መበሰራቸውን እንረዳለን።
የጀነት ነዋሪዎች ስፍራቸው ከመለያየቱና ደረጃቸው ከመበላለጡም ጋር ሁሉም ባሉበት ሁኔታ ደስተኞች እንደሚሆኑ እንረዳለን። ምክንያቱም ሁሉም በአንድ ቃል የሚመልሱት "ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸናል።" በማለት ነውና።