ትክክለኛውን አካሄድ ተከተሉ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ…

ትክክለኛውን አካሄድ ተከተሉ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ትክክለኛውን አካሄድ ተከተሉ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦች እንዲሰሩ፤ ወሰን ሳያልፉና ሳያጓድሉ በቻሉት ልክ አላህንም እንዲፈሩ፤ ስራቸው ተቀባይነት አግኝቶ በነርሱ ላይ የአላህ እዝነት እንዲወርድ ሰበብ እንዲሆንም በስራቸው ለአላህ በማጥራትና ሱናን በመከተል በትክክል መስራትን እንዲያስቡ አነሳሱ። ቀጥለውም ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው ብቻ አይድንም። ይልቁንም የግድ የአላህ እዝነት ያስፈልገዋል ብለው ነገሯቸው። ሰሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእርሶ ሥራ እንዲህ መጠኑ ከመግዘፉ ጋርም (መልካም ስራዎ ብቻውን) አያድኖትምን?" አሉ። እርሳቸውም "እኔም ብሆን አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እስካልሸፈነኝ ድረስ በስራዬ ብቻ አልድንም።" አሉ።

فوائد الحديث

ነወዊ እንዲህ ብለዋ፦ል "(ሰዲዱ ወቃሪቡ) ማለት ትክክለኛውን ፈልጉ፣ በትክክልም ስሩ፤ የተስተካከለ አድርጎ መስራትን ካልቻላችሁ ወደ ትክክለኛነት ቀረብ በሉ ማለት ነው። "ሰዳድ" ማለት በትክክል መስራት ማለት ነው። እርሱም ወሰን በማለፍና በማጓደል መካከል ያለ (ሚዛናዊውን) ነው። ስለዚህ ወሰን አትለፉም አታጓድሉም ማለት ነው።"

ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል፡ "መጥፎ ስራዎች እሳት የመግቢያ ምክንያት እንደሆኑ ሁሉ መልካም ስራዎችም ጀነት የመግቢያ ምክንያት ናቸው። ይህ ሐዲሥ ጀነት የሚገቡት በስራቸው ብቻ እንዳልሆነ ይገልጻል። ይልቁንም የግድ የአላህ ይቅር ባይነትና እዝነት ያስፈልጋቸዋል። እነርሱ የገቡት በስራቸው ምክንያት ቢሆንም ነገር ግን ይህንንም (በስራቸው ጀነት መግባትን ራሱ) ያስፈረደላቸው የአላህ እዝነት፣ ይቅር ባይነቱና ምህረቱ ነው።"

አንድ ባሪያ ስራው ምንም ያህል ቢደርስ ሊደነቅበትና ሊታለልበት አይገባም። ከርሱ ስራ ይልቅ የአላህ ሐቅ ይበልጣልና። ስለዚህም የትኛውም ባሪያ የግድ ፍራቻና ተስፋን አንድ ላይ መሰብሰብ ይገባዋል።

አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ችሮታና እዝነቱ ከስራቸው የበለጠ ሰፊ ነው።

መልካም ስራዎች ጀነት ለመግባት ምክንያት ቢሆኑም በርሷ ስኬታማ የሚኮነው ግን በአላህ ችሮታና እዝነት ነው።

ኪርማኒ እንዲህ ብለዋል፡ "ማንኛውም ሰው በአላህ እዝነት ካልሆነ በቀር ጀነት የማይገቡ ከሆነ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተለይተው የተጠቀሱበት ምክንያት እርሳቸው ጀነት እንደሚገቡ በቁርጥ የተረጋገጠ ከመሆኑም ጋር እርሳቸውም በአላህ እዝነት ካልሆነ በቀር ጀነት የማይገቡ ከሆነ ከርሳቸው ውጪ ያለውም ጀነት ሊገባ የሚችለው በአላህ እዝነት ሊሆን ይበልጥ የተገባ መሆኑን ለመጠቆም ነው።"

ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «{ትሰሩት በነበራችሁት ስራ ጀነት ግቡ።} [አንነሕል:32] {ይህቺም ያቺ ትሰሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ጀነት ናት።} [አዝዙኽሩፍ: 72] የሚለው የአላህ ንግግርና የመሳሰሉት ጀነት የሚገባው ሥራ በመስራት ምክንያት መሆኑን የሚጠቁሙ አንቀጾች የያዙት ሀሳብና የዚህ ሐዲስ ሃሳብ አይጣረሱም። ይልቁኑም የአንቀጾቹ ሀሳብ ጀነት የሚገባው በስራ ምክንያት መሆኑን የሚጠቁም ነው። ከዚያም ግን ለስራው መገጠም፣ በስራው ለአላህ ብቻ ብሎ ለመስራት መመራትና ስራውም ተቀባይነትን የሚያገኘው በአላህ እዝነትና ችሮታ ነው። ስለዚህም ትክክለኛው ጭብጥ በስራው ብቻ ጀነት አልገባም ነው። ሐዲሡ ሊገልፀው የፈለገው ሃሳብም ይህ ነው። በስራው ምክንያት ነው ጀነት የገባው ሊባል ይችላል። ይህም ግን ከአላህ እዝነት የመጣ ነው።»

ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ብለዋል: "በዚህ ዙሪያ አራት መልሶች ይገኛሉ: የመጀመሪያው: ለስራ መገጠም ራሱ ከአላህ እዝነት መሆኑ ነው። ቀዳሚ የሆነው የአላህ እዝነት ባይኖር ኖሮ ኢማን የሚባል፣ የሚድንበት የሆነው መልካም ስራም አይኖርም ነበር። ሁለተኛው: ባሪያ ለአሳዳሪው የሚያደርጋቸው ጥቅሞችና ስራዎች ሁሉ ለአለቃው የተገቡ ናቸው። አለቃው ለባሪያው ምንም ያህል ክፍያ ሰጥቶ ቢያጣቅመው ከችሮታው ነው። ሶስተኛው: አንዳንድ ሐዲሦች ውስጥ ጀነት መግባት በአላህ እዝነት እንደሆነና (በጀነት ውስጥ) የደረጃዎች ክፍፍል ግን በስራ መጠን እንደሆነ የሚጠቁም ገለፃም መጥቷል። አራተኛው: የአምልኮ ስራዎች ለጥቂት ዘመን የተሰሩ ሲሆኑ ምንዳው ግን ዘልአለሙን የማያልቅ ነው። በሚያልቅ ስራ የማያልቅ ፀጋና ምንዳ ማጣቀም በችሮታ የሚገኝ እንጂ ለስራ ክፍያ አይሆንም።"

አርራፊዒይ እንዲህ ብለዋል: «ማንኛውም ድርጊት ፈፃሚ ድርጊቱን የፈፀመው በአላህ መግጠም ወንጀልንም የተወው በአላህ ጥበቃ ነው። ይህ ሁሉ ደግሞ የአላህ ችሮታና እዝነት ነው። ስነዚህም አንድ ሰሪ መዳንን ለመፈለግና ደረጃዎችን ለማግኘት በስራው ላይ ሊመካ አይገባውም።»

التصنيفات

አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል