ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው…

ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው ጊዜ በአላህ ይጠበቅም ይከልከልም።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው ጊዜ በአላህ ይጠበቅም ይከልከልም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰይጣን አማኞችን ለመጎትጎት ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ፍቱን መድኃኒት ተናገሩ። "ይህን ማን ፈጠረው? ይህንንስ ማን ፈጠረው? ሰማይን ማን ነው የፈጠረው? ምድርንስ ማን ነው የፈጠረው?" በማለት ሰይጣን ጥያቄ ያቀርብልናል። አማኙም በእምነቱም ፣ በተፈጥሮውም፣ በአይምሮውም ተጠቅሞ "አላህ" በማለት ይመልስለታል። ሰይጣን ግን በዚህ የጉትጎታ ወሰን ላይ ከመቆም ይልቅ "ጌታህን ማን ፈጠረው?" ወደሚል የጉትጎታ ደረጃ ይሸጋገራል። በዚህ ጊዜ አንድ አማኝ ይህንን ጉትጎታ በሦስት ነገሮች ይከላከላል፦ በአላህ በማመን ከሰይጣን በአላህ በመጠበቅ ከጉትጎታው ጋር አብሮ መቀጠልን በማቆም

فوائد الحديث

የሰይጣንን ጉትጎታና ውልታ ችላ ማለት፤ ስለ እሱ ማሰብ እንደማይገባ እና ይህን ለማስወገድ ወደ አላህ መጠጋት የሚገባ መሆኑን።

ሁሉም በሰው ልጅ ቀልብ ውስጥ የሚከሰት ሸሪዐን ተፃራሪ የሆነ ጉትጎታ ከሰይጣን መሆኑን ፤

በአላህ ህልውና ጉዳይ ማስተንተን መከልከሉና ስለፍጡራኑና አንቀፆቹ ማስተንተን መበረታታቱን ተረድተናል።

التصنيفات

በአላህ ማመን, ኢስላም, አላህን የማውሳት ጥቅሞች