ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ

ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ

ዘይድ ቢን ኻሊድ አልጁሀኒይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሑደይቢያ ምሽት የዘነበን ዝናብ አስከትለው የንጋትን ሰላት አሰገዱን። ሰላቱን ያጠናቀቁ ጊዜም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ "ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ። በአላህ ችሮታና እዝነት ምክንያት ዘነበልን ያለ በኔ ያመነ በከዋክብት የካደ ነው። በእንዲህ እንዲህ የኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን ያለ ደግሞ በኔ የካደና በከዋክብት ያመነ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሑደይቢያ (መካ አቅራቢያ የምትገኝ መንደር ናት) የንጋት (የሱቢሕ) ሰላትን በዛ ምሽት ዝናብ ከዘነበ በኋላ አሰገዱ። ሰላቱን በማሰላመት ያጠናቀቁ ጊዜ ፊታቸውን ወደ ሰዎች በመዞር "የተከበረውና የላቀው ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" በማለት ጠየቋቸው። ሰሓቦችም አላህና መልክተኛው ያውቃሉ በማለት መለሱላቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ " ከፍ ያለው አላህ ሰዎች ዝናብ በሚዘንብ ወቅት ለሁለት እንደሚከፈሉ ገለፁ። አንዱ ክፍል በአላህ አማኝ የሆነ ክፍል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአላህ ከሀዲ የሆነ ክፍል ነው።" በአላህ ችሮታና እዝነት ዘነበልን በማለት የዝናብን መውረድ ወደ አላህ ያስጠጋ ሰው ይህ ፈጣሪና የዩንቨርሱ አስተናባሪ በሆነው አላህ ያመነ በከዋክብት ደግሞ የካደ መሆኑን፤ በእንዲህ እንዲህ ኮኮብ ዘነበልን ያለ ደግሞ በአላህ የካደና በከዋክብት ያመነ መሆኑን ገለፀ። ይህ ክህደት የዝናብን መውረድ ወደ ከዋክብት ከማስጠጋቱ አንፃር ትንሹ ኩፍር ነው። ምክንያቱም አላህ በሸሪዐም ሆነ በውሳኔ ዝናብ ለመዝነብ ሰበብ አላደረገውምና ነው። የዝናብን መውረድና ሌሎች ምድራዊ ክስተቶችን ከዋክብት ለመውጣትና ለማረፍ (ለመውደቅ) ወደሚያደርጉት እንቅስቃሴ ያስጠጋና ከዋክብት ትክክለኛ አስተናባሪ መሆናቸውን ያመነ ትልቁን ክህደት የካደ ይሆናል።

فوائد الحديث

ከዝናብ መውረድ በኋላ፦ በአላህ ችሮታና እዝነት ዘነበልን ማለት እንደሚወደድ።

የዝናብ መውረድና ሌሎችን ፀጋዎች መፍጠሩንም ሆነ ማስገኘቱን ወደ ከዋክብት ያስጠጋ ትልቁን ክህደት የካደ ሲሆን ወደ ከዋክብት በሰበብ ደረጃ ካስጠጋ ደግሞ ትንሹን ክህደት የካደ ይሆናል። ምክንያቱም ሸሪዐዊም ሆነ ህዋሳዊ ሰበብ አይደለምና።

አንድ ፀጋ በተካደ ጊዜ የክህደት ምክንያት ሲሆን፤ ተገቢ ምስጋና ከቀረበበት ደግሞ የኢማን ምክንያት ይሆናል።

የሽርክን መዳረሻ ለመዝጋት ሲባል ወቅቱን ለመግለፅ ተፈልጎበት ቢሆን እንኳን "በእንዲህ ኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን" ማለት መከልከሉ፤

ፀጋን በማምጣትና መአትን በመከላከል ረገድ ቀልብን በአላህ ላይ ማንጠልጠል ግዴታ መሆኑን ተረድተናል።

التصنيفات

አላህን በጌትነቱ መነጠል, ኢስላምን የሚያፈርሱ ነገሮች, የኢማን ቅርንጫፍ, ክህደት (ኩፍር)